Monday, September 7, 2015

የአለማችን ትልቁ የወንድ ብልት ግማሽ ሜትር ርዝመት አለው

አቶ ሮቤርቶ ኤስኪዩቬል ካብሬራ ነዋሪነቱን በሜክሲኮ ሳልቲሎ ውስጥ ያደረገ የ52 አመት ጎልማሳ ነው፡፡ ባልተለመደ መልኩ አለቅጥ የተለቀ ብልት ያለው አቶ ካብሬራ ከሰሞኑ ይህ ብልቱ ከአለም ትልቅ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ሲል ብልቱን ሚዛን ላይ አስቀምጦ አስመዝኖታል ሲል ሚረር ድረገጽ አስነብቧል፡፡
“በአለም ላይ ያለ የትኛውም ወንድ የኔን የሚያክል ብልት የለውም” የሚለው አቶ ካብሬራ፤ 48 ሳንቲሜትር ወይም ግማሽ ሜትር ገደማ የሚረዝም ብልቱን ነው ከሰሞኑ “ተመዝኖና ተለክቶ ከአለም አንደኝነቱ ይረጋገጥልኝ” ሲል ሚዛን ላይ ያስቀመጠው፡፡ ብልቱን ለመሸፈን በጨርቅ ጠቅልሎ ከሚዛን ላይ ያስቀመጠው አቶ ካብሬራ የብልቱ ክብደት 1 ኪሎ ገደማ ሆኖ መዝኗል፡፡
ብልቱ አለቅጥ ረዝሞ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ከጉልበቱ በታች ተንጠልጥሎ የሚታየው አቶ ካብሬራ፤ ምንም እንኳን ይህ የብልቱ መጠን በአለም አንደኛ ሆኖ እንዲመዘገብለት ቢፈልግም፤ “የብልቴ ባልተለመደ መልኩ መርዘምና መተለቅ የሴት ጓደኛ እንዳይኖረኝ አድርጎኛል… ሴቶች ከኔ ጋር ግብረስጋ የመፈጸም ፍላጎት ፈጽሞ የላቸውም እንዳውም ይፈሩኛል” ሲል ነው ብልቱ ችግር እንደሆነበት ያስረዳው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ከዚሁ ከብልቱ ርዝመት ጋር ተያይዞ “ስራ በአግባቡ እንዳልሰራም እያደረገኝ ስለሆነ አካል ጉዳተኛ ተብዬ መመዝገብ እፈልጋለሁ” ሲልም የብልቱ በጣም መርዘም ህይወቱን በአግባቡ እንዳይመራ ምን ያክል ጫና እያሳደረበት እንደሆነ ተናግሯል፡፡
የብልቱ መጠን ላይ ጥርጣሬ የሚያሳድሩ ሰዎች ያምኑት ዘንድ በህክምናም ለማረጋገጥ የፈለገው አቶ ካብሬራ ምርመራ አድርጎ ራጂ የተነሳ ሲሆን ውጤቱን ያዩት ዶክተሮችም በእርግጥም የአቶ ካብሬራ ብልት የውሸት አለመሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡ የአቶ ካብሬራ ግዙፍ ብልት ምንም እንኳ ግማሽ ሜትር ገደማ ቢረዝምም የብልቱ ዋና አካል እንደ አብዛኛው ጎልማሳ ሰው 15 ሳንቲሜትር ገደማ ብቻ እንደሆነና ሌላው ትርፍ አካል ግን ቆዳ እንደሆነም ነው የህክምና ባለሙያዎቹ የተናገሩት፡፡
አቶ ሮቤርቶ ኤስኪዩቬል ካብሬራ በአሜሪካ ይኖር የነበረ ቢሆንም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2011 ዓ.ም. እኛ በተለምዶ ተጠርዞ እንደምንለው ተይዞ ነው ወደ ሜክሲኮ ተመልሶ ሳልቲሎ ውስጥ መኖር የጀመረው፡፡ ወንድሞቹ በሰጡት አንድ ክፍል ውስጥ እየኖረ የሚገኘው ካብሬራ ህይወትን የሚመራው ከማህበራዊ ድጋፍ በሚያገኛት እርዳታና ከቆሻሻ ገንዳዎች ላይ ምግብ እየለቃቀመ ነው፡፡ ጓደኛ የሚባል ነገር እንደሌለው የሚናገረው ካብሬራ “በሄድኩበት ሁሉ ሰዎች ያገሉኛል” ሲልም የብልቱ ነገር ችግር እንደሆነበት ተናግሯል፡፡

ዳንኤል ቢሠጥ

2 comments: