ወዳጄ ዛሬ ዛሬ አለቅጥ መወፈር አደገኛ በሽታ ሆኖል፡፡
የበርካቶች የጤና ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ ድንቡሽቡሽ ብሎ መወፈር ያኔ የኑሮ ምቾትና የድሎት ምልክት ተደርጎ እንዳልተወሰደ
ሁሉ ዛሬ ደግሞ ሽንቅጥ ብሎ መታየት ብልህነትና የበርካቶች ምርጫ ሆኗል፡፡
ምናልባት አለቅጥ መወፈር አንድ ነገር በማስደረግ በኩል ብቻ
ጠቀሜታ ይኖረው ይሆናል ከተባለ ግን አሜሪካዊው “ዘ ቢግ ላ” ያደረገው ድርጊት ማሳያ ሆኖ የሚቀርብ ይመስለኛል፡፡ ቦርጩ ወርዶ
ወርዶ ከጉልበቱ የደረሰው “ዘ ቢግ ላ” አለቅጥ ሰብቶ የተንጠለጠለው ቦርጩን እንደምንም ጎትቶ ወደ ላይ ካነሳ በኋላ አንዲት
ሽጉጥ ቢጤ ከስሩ ሲያስቀምጥ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል፡፡
በእርግጥ ሽጉጥን ይዞ መዘዋወርም ሆነ አለቅጥ ሰብቶ
ህይወትን አደጋ ላይ መጣል ለማንም ቢሆን የሚመከር ባይንሆም ‘በስጋ የጨቀየው’፤ ወፍራሙ “ዘ ቢግ ላ” ግን ሁለቱንም ነገሮች
በአንድ ላይ ለማስኬድ ትንሽ ወጣ ያለ ሀዛብ ይዞ ብቅ ያለ ይመስላል፤ እንደ ሚረር ድረገጽ ዘገባ፡፡
No comments:
Post a Comment