በዳንኤል ቢሠጥ፡
ሀገረ ቻይና ፉጂያን ግዛት ሺሺ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ውሽምዬ የባልን
እቤት አለመኖር አጣርቶ ከሚስት ጋር ሊዳራ ከተፍ ብሏል፡፡ እናም አቶ ውሽማ የሰው ሚስት ሲማግጥ አቶ ባል ሳይጠበቅ እንደው ድንገት
ከሄደበት ቦታ ወደ ቤቱ ተመልሶ በር ማንኳኳት፤ ውሽማ ሆዬ ምን ውስጥ ይገባ! ያለው ሰባተኛ ፎቅ ላይ ነው! ቤቱ ያለው ደግሞ አንድ
በር ብቻ! እሱ ጋርም የልጂት ባል ክፈቺና አስገቢኝ እያለ ቆሟል፡፡ እንደ ዴይሊሜይል ድረገጽ ዘገባ፡፡
ይህን ጊዜ ነው ውሽምዬ “ባል አግኝቶ አንድ ነገር ከሚያደርገኝ
ይሄኛው ይሻለኛል” ሲል ሰባተኛ ፎቅ ላይ ካለው ቤት በመስኮት ወጥቶ የፎቁ ጠርዝ ላይ የቆመው፡፡ ካሁን አሁን ባል ይሄዳል በሚል
ተስፋም ሲጠባበቅ ይቆያል፡፡ አያ ባል ታዲያ ጉዳዩን ጨራርሶ መጥቶ ኖሮ እቤቱ አገር ሰላም ብሎ ይቀመጣል፤ አድሮም በጠዋት ወደ
ስራው ያመራል፡፡
ለሊቱን በሙሉ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ተገትሮ እንደቆመ “ካሁን አሁን
አንቀላፍቼ ወደቅኩ” በሚል ስጋት ተወጥሮ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ያደረው ውሽማ ታዲያ ነግቶ ባል ወደ ስራው ከሄደ በኋላ እንዴት
ብሎ ተመልሶ ወደ ቤቱ ይግባ፡፡ ማታ በመጠጥ ሀይልና ‘አያ ባል ይገድለኛል’ በሚል ፍራቻ ተደፋፍሮ የዘለለበትን መስኮት እንዴት
ብሎ ተመልሶ ይግባበት፡፡ ቆሞ የማደደር ድካሙ እንዳለ ሆኑ የመመለሻው ነገር ማጣፊያው ቢያጥረው ጊዜ ታዲያ በባሏ ላይ እየወሰለተች ያለችው ሚስት፤ መቼስ ያው ውሽማ ነውና
ሰባት ፎቅ ከምድር ከፍ ብሎ ጠርዝ ላይ የቆመው፤ የድረሱለት ጥሪ ለድንገተኛ አደጋ መከላከያ ሰዎች ስልኳን አንስታ ታስተላልፋለች፡፡
እርቃኑን አለመሆኑ እድለኛ ያደረገው ውሽማም በነብስ አድን ሰራተኞቹ
ገመድ ተጠፍሮ ማታ የዘለለበትን መስኮት እየተጎተተ ገብቶበት ህይወቱ ልትተርፍ ችላለች፡፡ “እኔ እዚህ ቦታ እንዴት እንደተገኘሁ
ምንም የማውቀው ነገር የለም” ብሎ ውሽሜ ቢሸመጥጥም ታዲያ የኋላ ኋላ በባሏ ላይ የወሰለተችው ሚስት ጉዳዩን አፍረጥርጣው የሆነውን
ሁሉ ተናዛለች፡፡
No comments:
Post a Comment