ወዳጄ መቼም በግልዎት ስራ የመጀመር ሀሳብ ይኖርዎታል፡፡ ጀምረውም
ከሆነ በደንብ አዋጪ የሆነ ካገኙ ገልበጥ ለማለት ሳያማትሩ እንደማይቀሩ እርግጥ ነው፡፡ ይበሉ እንግዲህ በወር 200 ሺ ብር ገደማ
የተጣራ ትርፍ የሚያስገኝ አዋጪ የሆነ የስራ ሃሳብ ልነግርዎት ነውና እስኪቢርቶና ወረቀት ቢጤ ያሰናዱ፡፡
ግን ከዚያ በፊት አሜሪካዊውን ስራ ፈጣሪ ላስተዋውቅዎት፡፡ አሌክስ
ክሬክ መኖሪያውን በአሜሪካ ቴክሳስ ያደረገ ስራ ፈጣሪ ነው፡፡ እንደ አብዛኛው ሰው የራሱን ስራ ጀምሮ ተፍ ተፍ እያለ መኖር ህልሙ
ነበር እናም ከለታት በአንዱ ቀን የሆነች የስራ ሀሳብ ብልጭ ስትልለት ቀድሞ ጉዳዩን ያማከራት ለፍቅረኛው ነበር፡፡ አሌክስ ሊሰራ
ያሰበውን ነገር የሰማችው ፍቅረኛው ሀሳብ ከማዋጣት ይልቅ ሳቅ ነበር የቀደማት፡፡ ፍርፍር እስክትል ሳቀች፤ በፍቅረኛዋ አዲስ የስራ
ፈጠራ ሀሳብ፡፡
የፍቅረኛውን ሳቅ ከቁብ ያልቆጠረው አሌክስ ከሀሳቡ ማፈግፈግ አልመረጠም፡፡
ይልቁንም ወደፊት ተራምዶ ህልሙን እውን ለማድረግ ነበር የወሰነው፡፡ እናም በስራው ስኬታማ መሆን ችሎ ዛሬ ላይ አሌክስ ሳቅ ከፍቅረኛው
ላይ ተረክቦ በሳቅ ፍርፍር እያለ ወደ ባንክ የሚያመራው እሱ ሆኗል፡፡ የአሌክስ ሥራ ፈጠራ ቀላል፤ እርሰዎ ወዳጄ ‘ደግሞ ይሄም
ስራ ነው!?’ ሊሉት የሚችሉ ግን ደግሞ እሱን ስኬታማ ያደረገውና በወር እስከ 200መቶ ሺ ብር እያሳፈሰው የሚገኝ ስራ ነው፡፡
እናልዎት ስራው ምን መሰልዎት የድንች ደብዳቤ ብለን ብንሰይመው የሚያስኬድ ሳይሆን አይቀርም፡፡
እንዴት መሰልዎት የ24 አመቱ ወጣት ስራ ፈጣሪ አሌክስ “ለሚፈልጉት
ሰው የሚፈልጉትን አጠር ያለ መልእክት ማንነትዎት ሳይገለጽ በድንች ላይ ጽፌ እሰድልዎታለሁ; እንደ ድንቹ መጠንም አስከፍልዎታለሁ”
የሚል የስራ ሀሳብ ይዞ ነበር የተነሳው፡፡ ይህን ሀሳቡንም ነበር ለፍቅረኛው እራት እየበሉ ያማከራት፤ ምንም እንኳ ከት ብላ ስቃ
“አንተ?… ብለህ ብለህ ደግሞ ምኑን ሀሳብ አመጣህው ባክህ? እኔ እዲህ ያለ የቄለ ሀሳብ ከዚህ ቀደም በህልሜም በእውኔም ሰምቼ
አላውቅም!.. እንደው አንተ ተሳክቶሎህ አንድ የድንች ደብዳቤ ከላክ ከምላሴ ድንች ይነቀል…!” ስትል ሀሳቡን ብታጣጥልበትም፡፡
የስራ ሀሳቡን በመረጃ መረብ ላይ ያንሸራሸረው አሌክስ ገና በሁለተኛው
ቀን ነበር “መልእክት አለን በድንች ደብዳቤ ላክልን” ከሚሉ ሰዎች የ40 ሺ ብር ውል መዋዋል የቻለው፡፡ “ይህ እንደሚሆን አውቅ
ነበር” ያለው አሌክስ እስካሁን ድረስ 2000 ያክል የደንበኞቹን የድንች መልእክቶችን መስደዱን ይናገራል፡፡ በዚህም በወር የተጣራ
200 ሺ ብር ማግኘት እንደቻለም ጭምር፡፡ “በመላው አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ የድንች ደብዳቤዎችን ልከናል፡፡ ምናልባትም ባልተለመደ
በልኩ!... እናም ደግሞ በበርካቶች ህይወት ላይ በበጎ መልኩ የሆነ ተጽእኖ ነገር አሳድረናል ለሽራፊ ሰከንድ እንኳ ቢሆንም ማለት
ነው፡፡” የሚለው አሌክስ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች መልእክት አለኝ እሱም…
“ሰዎች በህይወታቸው ወደ ኋላ የሚጎትቷቸው ሁለት ነገሮች አሉ እነሱም ፍርሀትና ጥርጣሬ ናቸው፡፡ እወድቃለሁ! ጊዜዬን በከንቱ ነው
የማባክነው የሚል ፍርሀትና ‘ይሳካልኝ ይሆን?’ የሚል ጥርጣሬ፡፡ እነዚህ መወገድ አለባቸው ብሏል፡፡”
100 ፊደላትን በሚይዙ መጠነኛ ድንቾች ላይ መልእክት እንዲሰፍርልዎት
ከፈለጉ አሌክስ 160 ብር ገደማ ያስከፍልዎታል፡፡ “አይ መልእክቴ በዛ ያለ ነው… ትልቅ ድንች ቢሆንልኝ እመርጣለሁ” ካሉ ደግሞ
140 ፊደላትን ሰድሮ ለሚይዝ ትልቅ ድንች 200 ብር ገደማ ለአሌክስ መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡ እሱም የሰጡትን መልእክት በጥቁር
መጻፊያ ፓርከር ድንች ላይ ጽፎ ስምዎት ሳይጠቀስ ለፈለጉት ሰው ያደርስልዎታል፡፡ እስካሁን ከተላኩ መልእክቶች መካከልም… “መልካም
የአባቶች ቀን” ሲል ልጅ ለአባቱ እንዲሁም የስራ እድገት ላገኘች እህቱ… “ኬሊ ለትልቁ ድንች እንኳን ደስ ያለሽ በጣም ተደንቸናል”
የሚሉ አዝናኝም ቁምነገር አዘልም መልእክቶች ይገኙበታል፡፡
እናም ወዳጄ… ምንም እንኳ ዛሬ ዛሬ መልእክትን በደብዳቤ የመላላክ
ልምዳችን እምብዛም እየሆነ ቢመጣም ምናልባት እርስዎ የደብዳቤ ተጠቃሚ ከሆኑና የሆነች ጽሁፍ ያረፈችባት ድንች በፖስታ ሳጥንዎት
ውስጥ ገብታ ቢያገኙ አንድ ወዳጅዎት በአሌክስ በኩል “ድንች በፖስታ ልኬልሃለሁ መልሱን በድንች እጠብቃለሁ…” ብሎ እያንጎራጎረ
መልእክቱን እንደሰደደልዎት ልብ ይበሉ፡፡ ቅድም ያሰናዷት እስኪቢርቶና ወረቀት ላይም ‘አዲስ የስራ ሀሳብ… የድንች ደብዳቤ… መነሻ
ካፒታል 20 ብር… መድረሻ ካፒታል በወር መጨረሻ 200 ሺ ብር!!!’ ብለው ይጻፉና አሁኑኑ ስራ ይጀምሩ፡፡
ዳንኤል ቢሠጥ
ለአዲስ ቴሌቪዥን እና ለኤፍ
ኤም 96.3
ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡
ReplyDelete